የጥራት ሥራ አመራር ሥርዓት (ISO 9001) ምንነትና ጥቅሞቹ
የጥራት ሥራ አመራር ሥርዓት (ISO 9001) ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው መለኪያ መስፈርት ሲሆን ምርቶች ወይምአገልግሎቶች የጥራት ደረጃቸው ዓለምአቀፍ ተቀባይነት እንዲኖረው ያስችላል፡፡እንዲሁም የስራ አገልግሎቱ ወይምምርቱ ደንበኛን በሚያረካ መልኩእንዲካሄድየአሠራር ሥርዓትን ተከትሎእንዲከወን የሚያስችል ሂደት ነው፡፡
የISO 9001 ዋናዋና ፋይዳዎች:-
- ለሁሉም ምቹ የውድድር መድረክ መክፈቱ
- የውጪ ንግድ እና ወይም አገልግሎት ማመቻቸቱ
- የተሻለ ተሞክሮን ማሳየቱ
- ለንግድእና ወይም አገልግሎት የብቃት አሰራርን ማሳየቱ
- መተማመን መፍጠሩ፤ እንዲሁም አዳዲስ የንግድ አማራጮች መያዙ
- የምርት መለያን በዓለም አቀፍ እንዲታወቅ ማድረጉ
- የጋራ መግባቢያ ቋንቋ በተቋም ውስጥም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ መፍጠር መቻሉ፡፡
ዓለም አቀፋዊ ዕውነታዎች
- ከ1,000,000 ድርጅቶች በላይ በአለም አቀፍ ደረጃ የISO 9001 ሰርቲፊኬት ተጠቃሚዎች ናቸው
- በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ያለው መሆኖ
- የተለያዩ ድርጅቶች የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ያደርጋል
- አንድ የሰው ኃይልያለው ተቋምም ቢሆን ሰርቲፈይድ መሆን ይችላል
Related Posts
ኢተምድ በመጀመሪያው ሩብ ዓመት 6,823 የአገልግሎት ጥያቄዎችን በማስተናገድ የጥራት ማረጋገጥ ሥራዎችን አከናውኗል፡፡
ኢተምድ ለአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የጥራት ሥራ አመራር ሥርዓት (ISO 9001:2015) ሰርተፊኬት ሰጠ።
ኢተምድ ለራህመት መሃመድ ዱቄት ፋብሪካ የጥራት ሥራ አመራር ሥርዓት (ISO 9001:2015) ሰርተፊኬት ሰጠ።