ኢተምድ የሚለው ምህፃረ ቃል ፡ የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት” ይወክላል፡፡ ኢተምድ በጥር ወር 2003ዓ.ም በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 196/2003 በፌደራል ደረጃ የመንግስት የልማት ድርጅት ሆኖ የተስማሚነት ምዘና አገልግሎቶችን ለመስጠት ተቋቁሟል፡፡ የድርጅቱ ተቆጣጣሪ ባለስልጣን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ነው፡፡
ኢተምድ በዋነኝነት የተስማሚነት ምዘና አገልግሎቶች ማለትም የላብራቶር ፍተሻ፣የኢንስፔክሽንና የሰርቲፊኬሽን አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን በስሩ ከ200 በላይ ሰራተኞችን ይዞ 8 ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶችን በመላው ሀገሪቱ በማደራጀት እየሰራ የሚገኝ ድርጅት ነው፡፡
የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው የፍተሻ ላቦራቶር፣የኢንስፔክሽንና ሰርቲፊኬሽን የአሰራር ሥርዓቶችን በመተግበር ተዓማኒነት ያለው፣ገለልተኛ፣ውጤታማ፣ተደራሽና ቀልጣፋ የተስማሚነት ምዘና አገልግሎት በመስጠት ጥራት ያለው ምርትና አገልግሎት እንዲኖር ማስቻልን ዓላማው አድርጎ የሚሰራ ድርጅት ነው፡፡
Related Posts
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን አመራርና ሠራተኞች ኢተምድን ጎበኙ፡፡
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር እና የተጠሪ ተቋማት የ2017 በጀት ዓመት የ9 ወራት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ ተካሄደ፡፡
የንግድና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በኢተምድ የመስክ ምልከታ አደረገ፡፡