ስለ ኢተምድ

የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት(ኢተምድ) በሰኔ ወር 2016ዓ.ም ድርጅቱን እንደገና ለማቋቋም በወጣው በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 549/2016 በፌደራል ደረጃ የመንግስት የልማት ድርጅት ሆኖ የተስማሚነት ምዘና አገልግሎቶችን ለመስጠት ተቋቁሟል፡፡ የድርጅቱ ተጠሪነት ለኢ.ፌ.ዴ.ሪ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር  ሚኒስቴር ነው፡፡

ኢተምድ በዋነኝነት የተስማሚነት ምዘና አገልግሎቶች ማለትም የላብራቶር ፍተሻ፣ የኢንስፔክሽንና የሰርቲፊኬሽን አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን በስሩ 240 ሰራተኞችን ይዞ 9 ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች በመላው ሀገሪቱ  በማደራጀት  እየሠራ  የሚገኝ ድርጅት ነው፡፡  በተጨማሪም  በጅቡቲ ወደብ ቅርንጫፍ በመክፈት የተስማሚነት ምዘና አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡

የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው የፍተሻ ላቦራቶር፣የኢንስፔክሽንና ሰርቲፊኬሽን የአሰራር ሥርዓቶችን በመተግበር ተዓማኒነት ያለው፣ገለልተኛ፣ውጤታማ፣ተደራሽና ቀልጣፋ የተስማሚነት ምዘና አገልግሎት በመስጠት ጥራት ያለው ምርትና አገልግሎት እንዲኖር ማስቻልን ዓላማው አድርጎ የሚሰራ ድርጅት ነው፡፡

ራዕይ                                                                     

ዓለም አቀፍ እውቅናና ተቀባይነት ያለው የተስማሚነት ምዘና አገልግሎት በመስጠት በአጋሮቻችን ተዓማኒና ቀዳሚ ተመራጭ ብሔራዊ ተቋም መሆን፣

ተልዕኮ

ዓለም አቀፍ እውቅናና ተቀባይነት ያለው የተስማሚነት ምዘና  እና የሥልጠና አገልግሎትን ለአምራቾችና ለአገልግሎት ሰጪዎች፣ለላኪዎች፣ ለአስመጪዎች እና ለተቆጣጣሪ አካላት በመስጠት ፍትሃዊ የንግድ ውድድር በማስፈን ተወዳዳሪ ኢኮኖሚ እንዲገነባ በመደገፍ የሸማቾችን ጤና እና የአካባቢ ደህንነትን መጠበቅ ነው፡፡

እሴቶች

ተጠያቂነት               – ሚስጥር ጠባቂነት

– ቀጣይነት ያለው መሻሻል      – ተዓማኒነት

–  አጋርነት                – ምላሽ ሰጪነት

–  አገልጋይነት